Quantcast
Channel: የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views
Browsing all 266 articles
Browse latest View live

ለሊዮ ቶሎይስቶይ የተጻፈ ደብዳቤ (እውነተኛ የሰሙኑ ገጠመኝ)

click here for pdf አንድ ወዳጄ ከሳምንታት በፊት አንድ ቴአትር ይጽፍና በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ቴአትር ቤቶች ወደ አንዱ ይሄዳል፡፡ ድርሰቱን ለግምገማ እንዲያስገባ ይነገረዋል፡፡ አስገባ፡፡ በቀደም ዕለት የግምገማውን ውጤት ለማየት ወደ ቤተ ተውኔቱ ያመራል፡፡ መዝገብ ቤቶቹም ‹የግምገማው ውጤት ደርሷል፡፡...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

እዝራ በእዝራ መንፈስ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ገጥመውን ከነበሩት ፈተናዎች አንዱ የሚያውቁት አለመጻፋቸውና የሚጽፉት አለማወቃቸው ነው፡፡ ባሕረ ጥበባት የተባሉት ሊቃውንት ትምህርታቸውን በቃል ከማስተማር ባለፈ በጽሑፍ አስቀምጠው ለማለፍ ብዙም አልተጉበትም፡፡ በዚህ የተነሣም በድርሰቱ ዓለም የምንጠቅሳቸውን ቀደምት...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ነፍሰ ጡሮች በኮርያ

 click here for pdf በኮርያ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ስትጓዙ ፒንክ ቀለም ያላቸውና በእንግሊዝኛ ‹ፒ› የሚል ፊደል የተጻፈባቸውን መቀመጫዎች ታገኛላችሁ፡፡ የነዚህ መቀመጫዎች ዓላማ ነፍሰ ጡር ሴቶች ያለ ችግር ወንበር እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ እንዲያውም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የተጀመረ...

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ፓንክረስት ሞተ ይላሉ

ፓንክረስት ሞተ ይላሉአያፍሩም ደግሞ ይዋሻሉ፤ታሪክን እንደነዳጅ ቆፍሮለቅርስ እንደ ውርስ ተከራክሮላልተወለደባት ምድር ከተወላጅ በላይ ለፍቶበደም ከወረሷት በላይ በፍቅር ልቧ ውስጥ ገብቶከእናቱ እስከ ልጁ - ለጦቢያ ልቡን ሠውቶበትውልድ ማማ ላይ ቆሞ የጸናውን ጌታሞቷል እያለ ይዋሻል ታሪክ የጠላ ቱማታ፡፡ኢትዮጵያዊነት...

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

የእንዳ ኢየሱስ ምሽግ፡- ከእቴጌ ጣይቱ እስከ ዶክተር ክንደያ

click here for pdfየመቀሌው ምሽግ ጥንታዊ ፎቶየአድዋ ጦርነትና ድል ሲነሣ ምንጊዜም አብሮ የሚነሣ የኢትዮጵያውያን የጀግንነትና የብልሃት ዐውደ ውጊያ አለ፡፡ የመቀሌው ምሽግ ውጊያ፡፡ጣልያኖች የመረብን ወንዝ ተሻግረው ወደ ትግራይ ሲገቡ ጠንካራ ምሽግ ከሠሩባቸው ቦታዎች አንዱ መቀሌ እንዳ ኢየሱስ ነበር፡፡...

View Article


ስሟ የጠፋው አህያ

click here for pdfየፊታችን እሑድ የሆሳዕና በዓል ይከበራል፡፡ ሆሳዕና የአህዮች ክብረ በዓል ነው፡፡ መቼም እንደ ዕለተ ሆሳዕና አህያ በታሪኳ የከበረችበት ቀን ያለ አይመስለኝም፡፡ ዙሪያዋን እየተዘመረ፣ ዘንባባ ተይዞ፣ ምንጣፍ ላይ እግሯ በኩራት እየተራመደ በኢየሩሳሌም ጎዳና ላይ ተጉዛለች፡፡ ከዚያ በኋላ ግን...

View Article

ለሕዝብ ያልታወቀ - ከሕዝብ የራቀ

መቅደላ ላይ ጀግናው ዐፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን የሠዉበትን ቦታ ለማየት ጎብኚዎች ተራራውን ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ እልፍ ብሎ ደግሞ አንድ የመቅደላ ገበሬ በትሩን ተደግፎ ቆሞ የሚሆነውን በአግራሞት ያያል፡፡ ይህንን የታዘበ ጋዜጠኛ ካሜራውን አነጣጥሮ፣ መቅረጸ ድምጹንም ወድሮ ጠጋ አለውና ‹ዐፄ ቴዎድሮስ የተሠዉበት የመቅደላ...

View Article

አራቱ መስተፃርራን

click here for pdf ኢትዮጵያ ውስጥ ለአንድ ሕዝብ የሚሠሩ፣ በአንድ መንግሥት የሚተዳደሩ የማይመስሉ ለመሥራት ተመሥርተው በማፍረስ የተጠመዱ አራት መስተፃርራን አሉ፡፡ እርስ በርሳቸው የሚቀዋወሙ፡፡ አንዱ የሠራውን ሌላው ካላፈረሰ የሠራ የማይመስለው፡፡ ዋና ተልዕኳቸው የሌላውን ማፍረስ እንጂ የራሳቸውን መሥራት...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ድስትና ሰሐን

 click here for pdfእሳቱን ግር አድርገው አንድደው ይለበልቡታል፡፡ ዕዳው የጀመረው ‹ትንሽ እሳት ይስማው› ብለው የጣዱት ጊዜ ነው፡፡ እሳቱ ሞቅ ሲያደርገው ሽንኩርቱን አቀመሱት፡፡ ሽንኩርቱ ብቻውን አልመጣም፡፡ ወደል ማማሰያ ይዞ እንጂ፡፡ ባልተወለደ አንጀቱ ሆዱን ያተራምስለት ገባ፡፡ አንዴ እያማሰለ፤ አንዴም...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

አምስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር

click here for pdfየበጎ ሰው  ሽልማት የዜና መግለጫአምስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር የእጩዎች ጥቆማ ግንቦት 16 ይጀመራልላለፉት አራት ዓመታት ለሀገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት አምስተኛው መርሐ ግብሩን ከነገ ግንቦት 16 ቀን...

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

የመርሕ ጥያቄ

click here for pdfሰሞኑን ዶክተር አባ ኃይለ ማርያም ኦርቶዶክሳውያን ካልሆኑ አካላት ጋር ያከናወኑትን ‹የጠበልና እምነት› ጉዳይ በተመለከተ አያሌ ጥያቄዎች ሲነሡ ነበር፡፡ ነገሩን ከየምንጮቹ ብሰማቸውም በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የነበረው የቂሣርያው ገዥ ፊስጦስ ‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣...

View Article

መማርና መማር (ሲጠብቅና ሲላላ)

click here for pdf ትዳርን የተቃናና የተሳካ ለማድረግ በሁለት ባላዎች ላይ መትከል ያሻል ይላሉ ሊቃውንቱ፡፡ በመማርና በመማር፡፡  ሰው ሌላውን ሥራ ሁሉ የሚሠራው አንድም ተምሮ አንድም ለምዶ ነው፡፡ ትዳር ሲመሠርት ግን ትምህርትም ልምድም የለም፡፡ ትዳርን እንደ ትምህርት ዓይነት መርጦ፣ ከፊደል እስከ ዳዊት...

View Article

ጥበበኛው ግንበኛ

click here for pdfግንበኛው ድንጋዩን ይጠርብና በድርድሩ ላይ ሰክቶ አንዴ ፈገግ፣ አንዴ ተከዝ፣ አንዴ ቆም አንዴም ጎንበስ ይላል፡፡ ላት አይቶ በግ እንደሚገዛ ሰው በግራ በቀኝ ያገላብጠዋል፡፡ እንደ ገዳም ጸሎት ሲመሰጥ፣ እንደ ጉብታ ዛፍ ሲናወጥ ይታያል፡፡ እንደ ኮከብ ቆጣሪ ሲያፈጥ፣ እንደ ጥሩ ወጥ ቀማሽ...

View Article


‹፣›

click here for pdf‹እኔኮ እዚህ ሀገር መኖር አልቻልኩም፡፡ በቃ ዝም ብለው ደስ ያላቸውን ሁሉ ነው እንዴ የሚያወሩት፡፡ አሁን ከነ እንትና ይኼ ይጠበቃል፡፡› እያለ በአራቱም አቅጣጫ መኪና እንደበዛበት የትራፊክ ፖሊስ እጁን በላይና በታች፣ በግራና በቀኝ እያወናጨፈ ወደ ቤቱ ገባ፡፡ ‹እኔኮ ምን...

View Article

በዓለ ወልድ የማነው?

አራት ኪሎ ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አጠገብ የሚገኘው የበዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ‹ልማት ላለማ ነው› ብሎ በዚያ ያረፉ ክርስቲያኖችን ዐጽም አንሡልኝ እያለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የፕሮፌሰር ዐሥራት ወልደየስን፣ ቀጥሎ የመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬን አሁን ደግሞ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ዐጽም አንሡ ብሏል፡፡...

View Article


የዮፍታሔና የአድማሱ ነገር

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬንና የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ዐጽም በተመለከተ የሰጠውን ማብራሪያ ተመለከትኩት፡፡ ካቴድራሉ ሐሳቡን ለማስረዳት መትጋቱን አደንቃለሁ፡፡ የካቴድራሉ ሐሳብ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት የራቀ በመሆኑ ግን ተገርሜያለሁ፡፡ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤና መልአከ ብርሃናት...

View Article

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ወደ ጵጵስናው የመጡት ብዙ ጫና ተደርጎባቸው ነበር፡፡ ከጵጵስናው ይልቅ በሶርያውያን ገዳም መኖርን ይመርጡ ነበር፡፡ ሺኖዳ የኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ምኞታቸው እንደ አባ ገብረ ክርስቶስ በበረሓ መኖር ነበር፡፡ የወቅቱ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ግን ገዳሙን እንዲረዱ ወደ ሶርያውያን ገዳም...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ማጥፋት፣ ለምን?

‹በአባታችን በዮሐንስ ከማ ዘመን ሃይማኖቱ የቀና ንጉሥ ይስሐቅ(1406-1421) ታላቅ ቤተ ክርስቲያን በእንጨትና በድንጋይ ያንጹ ዘንድ አዘዘ፡፡ ያቺም ቤተ ክርስቲያን ተሠርታ ስትፈጸም ፈረሰች፡፡ ንጉሡም ይህንን ሰምቶ እጅግ አዘነ፡፡ እንዲህ ሲልም ወደ አባ ዮሐንስ ከማ መልእክት ላከ፤‹‹የዚህን ነገር ምክንያት ታውቅ...

View Article

‹ድኻ ወርቅ አይግዛ›

‹ድኻ ወርቅ አይግዛ ከገዛም ይጥፋበት› ይላሉ የምንዳዬ እናት አባዬ፡፡ ‹ምነው አባዬ ድኻ በመከራ የገዛውን ወርቅ እንዴት ይጥፋበት ይላሉ› ብለን ሞገትናቸው፡፡ ‹እይውልህ እኛ ሠፈር አራት ኪሎ አዲሴ የሚሏት አንዲት ጎረቤታችን ነበረች፡፡ ቁርስ፣ ምሳና እራት የተዘበራረቁባት፡፡ ለነገሩ ላለው ነው እንጂ ለሌለው ሰው...

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

የ፳፻፱ ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች

                                መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ1.    ዶ/ር መስፍን አርአያ (ለብዙ ዓመታት የዐማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ የአእምሮ ሕክምና ባለሞያ)  2.   አቶ ገመቹ ዲቢሶ(ዋናው ኦዲተር)3.   አቶ ማቴዎስ አስፋው(የአዲስ አበባ ፕላን...

View Article
Browsing all 266 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>